Kebede Yimer
Department of English Language and Literature, Debre Berhan University, P.O. Box 445, Debre Berhan, Ethiopia
Abstract
የዚህ ጥናት ዓላማ በ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የመማር እና የማስተማር መስተጋብር ላይ ከሥነትምህርታዊ ዲስኩር አኳያ ትንተና ማድረግ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት በደብረብርሃን ከተማ በሚገኙ አራት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስድስት የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በአመቺ የንሞና ዘዴ በመምረጥ በክፍል ውስጥ ሲያስተምሩ
በድምፅ እና ምሥል መቅረጫ አማካኝነት
የ18 ክፍለጊዜ መረጃ ተሰብስቧል፤ ተቀረጿል፡፡
መረጃው ወደ ምዝግብ መረጃነት ከተቀየረ
በኋላም በንግግር ልውውጥ ትንተና ዘዴ መሠረት ተተንትኗል፡፡
የትንተናው ውጤትም የማስተናበሪያ
እና የማስተማሪያ ዲስኩሮች
የአወቃቀር ሥርዓት የአቃፊ እና የታቃፊ ቅንጅት እንደሆነ
አመልክቷል፡፡ ይህም የማስተናበሪያ
ዲስኩር አቃፊ ሲሆን የማስተማሪያ ዲስኩር ታቃፊ መሆኑን አሳይቷ፡፡ ነገር ግን የማስተናበሪያ
ዲስኩር አቃፊ ሊሆን የሚችለው በእርእሰ
ጉዳዩ መቋጫ ላይ ሲከሰት ነው፡፡ ከአገልግሎት አኳያም የማስተናበሪያ ዲስኩር የማስተማሪያ ዲስኩር በተቀላጠፈ መልኩ ይካሄድ ዘንድ እገዛ አደርጓል፡፡
በተጓዳኝ የማስተማሪ ዲስኩር የቋንቋ ትምህርቱ
ማቅረቢ
ሚዲያ በመሆን አገልግሏል፡፡ ስለዚህ መምህሩ በሚያስተምረው የትምህርት
ዓይነት ላይ ያለውን ብቃት ለመገምግም
መተኮር ያለበት በማስተማሪያ
ዲስኩሩ ላይ ነው፡፡ ነገር ግን በክፍል አመራር ችሎታው ላይ ከሆነ በማስተናበሪያ
ዲስኩሩ ላይ መሆን እንዳለበት ይህ ጥናት ይጠቁማል፡፡
Keywords: ትምህርታዊ ዲስኩር፣ የማስተናበሪያ ዲስኩር፣ የማስተማሪያ ዲስኩር፣ የንግግር ልውውጥ
Author Biographies
Kebede Yimer, Department of English Language and Literature, Debre Berhan University, P.O. Box 445, Debre Berhan, Ethiopia